Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 22:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ኢያ​ሱም መሠ​ዊ​ያ​ውን “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምስ​ክር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆነ ይህ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ምስ​ክር ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የሮቤልና የጋድ ወገኖችም፣ እግዚአብሔር አምላክ ለመሆኑ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው፤ በማለት መሠዊያውን “ምስክር” ብለው ጠሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ “ጌታ አምላክ እንደሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው” ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 22:34
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ነገር ግን በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ኛም በኋላ በት​ው​ል​ዳ​ች​ንና በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና በቍ​ር​ባን፥ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም እን​ዳ​ይሉ ምስ​ክር ይሆ​ናል።


ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ።


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ይህች ድን​ጋይ በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር ናት፤ እር​ስዋ፥ ዛሬ እንደ ነገ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ለ​ውን ሁሉ ሰም​ታ​ለ​ችና በኋላ ዘመን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ክ​ዱት ይህች ድን​ጋይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለች” አላ​ቸው።


ላባም፥ “ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ትሁን” አለው። ላባም “ወግረ ስምዕ” ብሎ ጠራት፤ ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲሁ አላት።


ላባም፥ “ይህች ያቆ​ም​ኋት የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ዛሬ ምስ​ክር ናት” አለ። ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ።


በዚያ ቀን በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል አን​ዲቱ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ትሆ​ና​ለች፤ በዳ​ር​ቻ​ዋም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ዐ​ምድ ይሆ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች