Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ይል​ቁ​ንም ከል​ባ​ችን ፍር​ሀት የተ​ነሣ፦ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ምን አላ​ችሁ? እን​ዳ​ይ​ሉ​አ​ቸው ስለ​ፈ​ራን ይህን የሠ​ራ​ነው ካል​ሆነ፥ እና​ንተ የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እኛማ ይህን ያደረግነው፣ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ለዘሮቻችን እንዲህ እንዳይሏቸው ፈርተን ነው፤ ‘ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ ምን ግንኙነት አላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ይልቁንም ይህን ያደረግነው ከልባችን ፍርሃት የተነሣ ሲሆን እንዲህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ‘ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ጋር ምን ነገር አላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እኛ የሠራነው ለዚህ አይደለም፤ እኛ እርሱን የሠራነው በሚመጡት ዘመናት የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘እናንተ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን ግንኙነት አላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 22:24
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


ስለ​ዚ​ህም በፊ​ትህ ያለ​ውን ደመ​ወ​ዜን ለመ​መ​ል​ከት በመ​ጣህ ጊዜ ወደ​ፊት ጻድ​ቅ​ነ​ቴን ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል፤ ከፍ​የ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ የሌ​ለ​በት፥ ከበግ ጠቦ​ቶ​ችም ጥቁር ያል​ሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰ​ረቀ ይቈ​ጠ​ር​ብኝ።”


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤


“ነገ ልጅህ፦ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድስ ምን​ድን ነው? ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥


አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ድ​ን​ክ​ደው፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ልን ቍር​ባን እን​ድ​ና​ሳ​ር​ግ​በት፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እን​ድ​ና​ቀ​ር​ብ​በት መሠ​ዊያ ሠር​ተን እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ራሱ ይመ​ራ​መ​ረን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖ​ስን ድን​በር አድ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ሁም ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ም​ለክ እን​ዳ​ያ​ወ​ጡ​አ​ቸው ብለን ይህን አደ​ረ​ግን።


እነ​ዚ​ህም ምል​ክት ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥ ልጅ​ህን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች