Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር ዳርቻ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ ባለው በገ​ለ​ዓድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባሉ​በት ወገን፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ መሠ​ዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእስራኤላውያን ይዞታ በሆነችው በከነዓናውያን ምድር ወሰን በገሊሎት ላይ የሮቤልና የጋድ፣ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ መሠዊያ መሥራታቸውን ሌሎቹ እስራኤላውያን በሰሙ ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የእስራኤልም ልጆች እንዲህ የሚል ወሬ ሰሙ፦ “እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርተዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቀሩትም የእስራኤል ሕዝብ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ ያሉት የምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር በምትገኘው በእስራኤላውያን ይዞታ በሆነችው በገሊሎት መሠዊያ መሥራታቸውን ሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርተዋል የሚል ወሬ ደረሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 22:11
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት በነ​በ​ረው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በቢ​ታ​ንያ በቤተ ራባ እን​ዲህ ሆነ።


ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዉ ቀን ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት በማ​ለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃ​ብር መጣች፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም ከመ​ቃ​ብሩ አፍ ተነ​ሥቶ አገ​ኘ​ችው።


ሁለት መላ​እ​ክ​ት​ንም ነጭ ልብስ ለብ​ሰው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ሥጋ በነ​በ​ረ​በት ቦታ አንዱ በራ​ስጌ፥ አን​ዱም በግ​ርጌ ተቀ​ም​ጠው አየች።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።


በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ አቅ​ራ​ቢ​ያም ወደ ገለ​ዓድ በመጡ ጊዜ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዚያ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ የሚ​ታይ ታላቅ መሠ​ዊያ ሠሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ሁሉ የሚ​ለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠ​ዊ​ያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ ትክ​ዱት ዘንድ ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀጢ​አት ምን​ድን ነው?


ነገር ግን የር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቢያ​ን​ሳ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ምድር አል​ፋ​ችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጭ ለእ​ና​ንተ መሠ​ዊያ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ካዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አት​ተ​ዉት።


የገ​ለ​ዓድ ሰዎ​ችም ኤፍ​ሬም በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ደረ​ሱ​ባ​ቸው። ከዚህ በኋላ ከኤ​ፍ​ሬም ያመ​ለ​ጡት እን​ሻ​ገር ባሉ ጊዜ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እና​ንተ ከኤ​ፍ​ሬም ወገን ናች​ሁን?” ቢሉ​አ​ቸው “አይ​ደ​ለ​ንም” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች