Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ምድ​ሩ​ንም ሁሉ በየ​ድ​ን​በሩ ርስት እን​ዲ​ሆን ከፍ​ለው ከጨ​ረሱ በኋላ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርስት ሰጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 እስራኤላውያን ድርሻ ድርሻቸውን ከያዙ በኋላ፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ምድሩንም ሁሉ በየግዛቱ ርስት እንዲሆን አከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 እስራኤላውያን ምድሪቱን ተከፋፍለው በጨረሱ ጊዜ ለነዌ ልጅ ኢያሱ ከምድሪቱ ከፍለው ርስት ሰጡት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:49
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዳን ልጆ​ችም ሄደው ለኪ​ስን መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ቸ​ው​ንም ያዟት፤ በሰ​ይ​ፍም መቱ​አት። በው​ስ​ጥ​ዋም ተቀ​መጡ። ስሟ​ንም በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም በኤ​ዶ​ምና በሰ​ላ​ሚን ለመ​ኖር ቀጠሉ። የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ በረ​ታች። ገባ​ሪ​ዎ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።


በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።


በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች