Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሌዋውያኑ ግን ለእግዚአብሔር የሚሰጡት የክህነት አገልግሎት ርስታቸው ስለ ሆነ በእናንተ መካከል ድርሻ አይኖራቸውም። ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምሥራቅ ዮርዳኖስ የሰጣቸውን ርስት ቀደም አድርገው ወስደዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ነገር ግን የጌታ ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ ድርሻ የላቸውም፤ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የጌታ ባርያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይሁን እንጂ የሌዋውያን ድርሻ ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን ማገልገል ስለ ሆነ እነርሱ ከሌሎቻችሁ ጋር የርስት ድርሻ አይኖራቸውም፤ የሮቤልና የጋድ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት አስቀድመው ወርሰዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ እድል ፈንታ የላቸውም፥ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 18:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “በም​ድ​ራ​ቸው ርስት አት​ወ​ር​ስም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ድርሻ አይ​ሆ​ን​ል​ህም፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ህና ርስ​ትህ እኔ ነኝ።


ሌዋ​ው​ያን ግን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ይሥሩ፤ እነ​ር​ሱም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አይ​ወ​ር​ሱም።


አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”


ስለ​ዚህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ክፍ​ልና ርስት የላ​ቸ​ውም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች