Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ድን​በ​ሩም ከዚያ በደ​ቡብ በኩል ቤቴል ወደ​ም​ት​ባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድን​በ​ሩም በታ​ች​ኛው ቤቶ​ሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአ​ጣ​ሮ​ቶ​ሬክ ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያ ደግሞ ወደ ደቡብ ሎዛ ማለት ወደ ቤቴል ተረተር ይሻገርና በታችኛው ቤትሖሮን በስተ ደቡብ ባለው ተራራ በኩል አድርጎ ወደ አጣሮት አዳር ይወርዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል በሎዛ አቅጣጫ ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ወገን አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይኸው ድንበር በደቡብ በኩል ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ ወደነበረችው ወደ ቤትኤል ይወጣና በታችኛው ቤትሖሮን ተራራ በኩል ወደ ዐጣሮትአዳር ይወርዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ፥ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 18:13
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም ያን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስ​ቀ​ድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።


ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ድን​በር በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ደ​ዚህ ነበረ፤ የር​ስ​ታ​ቸው ድን​በር ከአ​ጣ​ሮ​ትና፥ ከኤ​ሮሕ ምሥ​ራቅ ከጋ​ዛራ እስከ ላይ​ኛው ቤቶ​ሮን ድረስ ነበረ፤


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።


ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ።


ሁለ​ተ​ኛው ክፍል ወደ ቤቶ​ሮን መን​ገድ ዞረ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ክፍል በገ​ባ​ዖን መን​ገድ ባለው ወደ ሴቤ​ሮም ሸለቆ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በዳ​ር​ቻው መን​ገድ ዞረ።


ቤተ ባራ፥ ሰራ፥ ቤስና፤


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማ​ኬ​ማስ፥ በአ​ያል፥ በቤ​ቴ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች