Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ አጠ​ገብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ኢያ​ቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወ​ጣል፤ ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባ​ሕር በኩል ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ይወ​ጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፥ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 15:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ተራራ መጨ​ረሻ ወረደ፤ እር​ሱም በራ​ፋ​ይም ሸለቆ በሰ​ሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያ​ቡስ ዳር በደ​ቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምን​ጭም ወረደ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ሰው​ዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማ​ደር አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወደ ተባ​ለ​ችው ወደ ኢያ​ቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት የተ​ጫኑ አህ​ዮች ነበሩ፤ ዕቅ​ብ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረች።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ባል የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ከተ​ማና የኢ​ያ​ሪ​ሞን ከተማ ገባ​ዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። የብ​ን​ያም ልጆች ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት እን​ዲ​ሠዋ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነ​በ​ረ​ውን ጣፌ​ትን ርኩስ አደ​ረ​ገው።


ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የብ​ን​ያም ልጆች አላ​ወ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ኤር​ም​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትን​ቢት ሊና​ገር ወደ​ዚያ ልኮት ከነ​በ​ረው ስፍራ ከቶ​ፌት ተመ​ለሰ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፦


ስለ​ዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእ​ርድ ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በከ​ር​ሲት በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚ​ያም የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል አን​ብብ፤ እን​ዲ​ህም በል፦


አጫጅ የቆ​መ​ውን እህል ሰብ​ስቦ ዛላ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ጭድ ይሆ​ናል፤ በሸ​ለቆ እሸ​ትን እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


ደግ​ሞም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለም​ስሉ ሠዋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛ​ብም ክፉ ልማድ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ መጡ፤ ወደ ረዓ​ይ​ትም ሸለቆ ወረዱ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው በረ​ዓ​ይት ሸለቆ ተበ​ት​ነው ሰፈሩ።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ተዋ​ግ​ተው ያዙ​አት፤ በሰ​ይፍ ስለ​ትም መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።


ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ኢያ​ቡስ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ በሀ​ገ​ሩም የተ​ቀ​መጡ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን በዚያ ነበሩ።


በዛ​ኖህ፥ በዓ​ዶ​ላም፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ በለ​ኪ​ሶና በእ​ር​ሻ​ዎ​ችዋ፥ በዓ​ዜ​ቃና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ተቀ​መጡ። እን​ዲሁ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች