ኢያሱ 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በሸለቆው በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ታጠፈ፤ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ ማብቂውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ተነሥቶ ወደ ዳቢር ይወጣል፤ በሰሜን በኩልም አድርጎ ወደ ጌልጌላ ይመለሳል፤ እርሱ ከአዱሚም ትይዩ ይኸውም ከሸለቆው በደቡብ በኩል ነው፤ ስለዚህ ድንበሩ በኤንሼሜሽ ምንጭ በኩል ያልፋል፤ መጨረሻውም ኤን ሮጌል ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በወንዙ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ተመለከተ፥ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፥ ምዕራፉን ተመልከት |