Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 15:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 15:47
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ አጽ​ሞ​ንም ያል​ፋል፤ በግ​ብ​ፅም ሸለቆ በኩል ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።”


ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፣ አዛጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።


ቡሀ​ነት በጋዛ ላይ መጥ​ቶ​አል፤ አስ​ቀ​ሎና ጠፋች፤ የዔ​ናቅ ቅሬ​ታ​ዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላ​ች​ሁን ትነ​ጫ​ላ​ችሁ?


ፈር​ዖ​ንም ጋዛን ሳይ​መታ ስለ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከአ​ቃ​ሮ​ንና ከጌ​ምና ጀምሮ በአ​ሴ​ዶት አቅ​ራ​ቢያ ያሉ ሁሉና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤


የሳ​ምር ተራ​ራ​ዎች ፥ ኢዩ​ቴር፥ ሦካ፤


እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ።


በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጋዛና እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ፥ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ምሽጉ ከተማ ድረስ አጠፋ።


ወጥ​ቶም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ የጌ​ትን ቅጥር፥ የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ቅጥር፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ በአ​ዛ​ጦ​ንና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ከተ​ሞ​ችን ሠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች