Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ የአ​ር​ቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የዔ​ና​ቃ​ው​ያን ዋና ከተማ ነበ​ረች። ምድ​ሪ​ቱም ከው​ጊያ ዐረ​ፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው ሰው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባዕ ነበር፤ ይህም አርባዕ ከዐናቃውያን መካከል ታላቅ ሰው ነበር። ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያትአርባቅ ትባል ነበር፥ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ከሁሉ ከፍ ያለ ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 14:15
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አር​ባቅ በም​ት​ባል ከተማ ሞተች፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር ያለች ኬብ​ሮን ናት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ለሣራ ሊያ​ዝ​ን​ላ​ትና ሊያ​ለ​ቅ​ስ​ላት ተነሣ።


ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ውን ሰጠው፤ ኢያ​ሱም የዔ​ናቅ ዋና ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ሰጠው። እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት።


ምድ​ያ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ዳግ​መኛ አላ​ነ​ሡም፤ በጌ​ዴ​ዎ​ንም ዕድሜ ምድ​ሪቱ አርባ ዓመት ዐረ​ፈች።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


በዚ​ያም ወራት ሞዓ​ባ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ገቡ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰማ​ንያ ዓመት ዐረ​ፈች። ናዖ​ድም እስ​ኪ​ሞት ድረስ ገዛ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ፥ አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ እን​ግ​ዶች ሆነው ወደ ተቀ​መ​ጡ​ባት በአ​ር​ባቅ ከተማ ወደ​ም​ት​ገ​ኘው ወደ መምሬ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ወደ​ም​ት​ባ​ለው መጣ።


እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ስለ ተከ​ተለ ኬብ​ሮን እስከ ዛሬ ለቄ​ኔ​ዛ​ዊው ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ርስት ሆነች።


የኤ​ናቅ ልጆች ከተማ ቅር​ያ​ት​ያ​ር​ቦ​ቅ​ንና በዙ​ሪ​ያዋ ያሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሰጡ​አ​ቸው፤ ይህ​ች​ውም በይ​ሁዳ ተራራ ያለች ኬብ​ሮን ናት።


ስለ መን​ደ​ሮ​ቹና ስለ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ከይ​ሁዳ ልጆች ዐያ​ሌ​ዎች በቂ​ር​ያ​ት​አ​ር​ባ​ቅና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በዲ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥ በቃ​ጽ​ብ​ኤ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥


ኢያ​ሱም የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን እርሻ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ልጆች ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው።


ሙሴም እንደ ተና​ገረ ለካ​ሌብ ኬብ​ሮ​ንን ሰጡት፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ከተ​ሞ​ችን ወረሰ፤ ከዚ​ያም ሦስ​ቱን የዔ​ናቅ ልጆች አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው።


በኬ​ብ​ሮን ለነ​በሩ፥ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​መ​ላ​ለ​ሱ​በት ስፍራ ለነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ላከ።


አል​ዓ​ዛር ፊን​ሐ​ስን ወለደ፤ ፊን​ሐ​ስም አቢ​ሱን ወለደ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች