Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴም በላ​ከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበ​ርሁ፥ ዛሬም ገና እን​ዲሁ ለመ​ዋ​ጋት ለመ​ው​ጣ​ትም ለመ​ግ​ባ​ትም ጽኑዕ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም ዐብሮኝ አለ፤ ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድ፣ ለመውጣትም ለመግባትም ኀይሉም ብርታቱም አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 14:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ፥ ምድ​ርን መሠ​ረ​ታት፥ አጸ​ና​ትም።


አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ፥ እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተና​ገ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አርባ አም​ስት ዓመ​ታት በሕ​ይ​ወት አኖ​ረኝ፤ አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሆነኝ።


ጫማህ ብረ​ትና ናስ ይሆ​ናል፤ እንደ ዕድ​ሜህ እን​ዲሁ ኀይ​ልህ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች