Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ዕለት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አልነበረም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተዋግቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፊ​ታ​ችሁ የሚ​ሄ​ደው አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በግ​ብፅ ምድር እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ሁሉ፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮ​አ​ችሁ ይዋ​ጋል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ስለ እና​ንተ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ እና​ንተ የተ​ዋጋ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣት ታህል እም​ነት ብት​ኖ​ራ​ችሁ ይህ​ችን ሾላ ከሥ​ርሽ ተነ​ቅ​ለሽ በባ​ሕር ውስጥ ተተ​ከዪ ብት​ሉ​አት ትታ​ዘ​ዝ​ላ​ች​ኋ​ለች።”


እነሆ፥ በአ​ባ​ትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀ​ሐይ ጋራ የወ​ረ​ደ​ውን በደ​ረ​ጃ​ዎች ያለ​ውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እን​ዲ​መ​ለስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።” ፀሐ​ይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወ​ረ​ደ​በት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።


ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።


እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች