Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአንደበትህ አይለይ፥ ነገር ግን በእርሱ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ እንድትጠብቅና እንድታደርገው በቀንም በሌሊትም አሰላስለው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቃናልሃል ይከናወንልሃልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፥ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 1:8
40 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።


የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃሎች ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።”


እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።


“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።


ይህ​ንም ዐው​ቃ​ችሁ ብት​ሠሩ ብፁ​ዓን ናችሁ።


አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል።


ታደ​ር​ገው ዘንድ ቃሉ በአ​ፍ​ህና በል​ብህ፥ በእ​ጅ​ህም ውስጥ ለአ​ንተ እጅግ ቅርብ ነው።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላ​ካ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ችሁ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።


እስ​ራ​ኤል ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመ​ረ​ጠው ቦታ በአ​ን​ድ​ነት በሚ​ሄ​ድ​በት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በጆ​ሮው አን​ብ​በው።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።


አንተ ግን አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ አስ​ነ​ሣኝ።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


ይስ​ሐ​ቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያ​ሰ​ላ​ሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይ​ኖ​ቹ​ንም አቀና፤ እነ​ሆም ግመ​ሎች ሲመጡ አየ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች እስከ መጨ​ረሻ በመ​ጽ​ሐፍ ጽፎ ከፈ​ጸመ በኋላ፥


ከዚ​ህም በኋላ ኢያሱ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ፥ የሕ​ጉን ቃሎች ሁሉ በረ​ከ​ቱ​ንና ርግ​ማ​ኑን አነ​በበ።


ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች