Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሊ​ባ​ኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግ​ቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰ​ና​ችሁ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የርስታችሁ ዳርቻ ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከታላቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ አንሥቶ፣ የኬጢያውያንን ምድር በሙሉ ይዞ፣ በምዕራብ በኩል እስከ ታላቁ ባሕር ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ፥ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ግዛታችሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስክ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 1:4
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አን​ዱም ሰረ​ገላ በስ​ድ​ስት መቶ፥ አን​ዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ብር ከግ​ብፅ ይወጣ ነበር። እን​ዲ​ሁም ለኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥ​ታ​ትና ለሶ​ርያ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በባ​ሕሩ በኩል ያወ​ጡ​ላ​ቸው ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


በገ​ለ​ዓድ ምድር እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው በዝ​ተው ነበ​ርና በም​ሥ​ራቅ በኩል ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድረ በዳው መግ​ቢያ ድረስ ተቀ​መጠ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ተመ​ል​ሳ​ችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞ​ራ​ው​ያን ተራራ፥ ወደ አረ​ባም ሀገ​ሮች ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ውም፥ በሜ​ዳ​ውም፥ በሊ​ባም፥ በባ​ሕ​ርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ ወደ ሊባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ ሂዱ።


የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።


እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።


መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው፤” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች