Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “የነገርከንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 1:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።


አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።


የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም ሙሴን እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጌታ​ችን እን​ዳ​ዘዘ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።”


በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች