Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮናስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይህ ወሬ ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፥ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፥ ማቅ ለበሶ በአመድም ላይ ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የነነዌ ንጉሥ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሰ መንግሥቱንም በማውለቅ ማቅ ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮናስ 3:6
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቍስ​ሉ​ንም ያክ​ክ​በት ዘንድ ገል ወሰደ፥ ከከ​ተ​ማም ወጥቶ በአ​መድ ላይ ተቀ​መጠ።


“ኮራዚ ወዮ​ልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮ​ልሽ! በእ​ና​ንተ የተ​ደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ተደ​ርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብ​ሰው አመ​ድም ነስ​ን​ሰው በተ​ቀ​መጡ ንስ​ሓም በገቡ ነበር።


“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።


የሕ​ዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራ​ስ​ሺም ላይ አመድ ነስ​ንሺ፥ አጥፊ በላ​ያ​ችን በድ​ን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ና​ልና ለተ​ወ​ዳጅ ልጅ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አል​ቅሺ።


ለነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና ለመ​ኳ​ን​ንቱ፦ የክ​ብ​ራ​ችሁ አክ​ሊል ከራ​ሳ​ችሁ ወር​ዶ​አ​ልና ራሳ​ች​ሁን አዋ​ር​ዳ​ችሁ ተቀ​መጡ በላ​ቸው።


በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።


ተስፋ ይሆ​ነው እንደ ሆነ አፉን በአ​ፈር ውስጥ ያኑር።


ስለ​ዚህ ራሴን እን​ቃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ቀለጠ። እኔ አፈ​ርና አመድ እንደ ሆንሁ አው​ቃ​ለሁ።”


በየ​መ​ን​ገ​ድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየ​ሰ​ገ​ነ​ቶ​ች​ዋም አል​ቅሱ፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ዋም እን​ባን እጅግ እያ​ፈ​ሰ​ሳ​ችሁ ወዮ በሉ።


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው።


የባ​ሕ​ርም አለ​ቆች ሁሉ ከዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ ዘው​ዳ​ቸ​ውን ከራ​ሳ​ቸው ያወ​ር​ዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያወ​ል​ቃሉ፤ በመ​ሬ​ትም ላይ ተቀ​ም​ጠው ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ራሉ፤ ስለ አን​ቺም ያለ​ቅ​ሳሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸ​ውም ወጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ሁለት ትና​ንሽ የፍ​የል መን​ጋ​ዎች ሆነው በፊ​ታ​ቸው ሰፈሩ፤ ሶር​ያ​ው​ያን ግን ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋት ነበር።


ሚክ​ያ​ስም ባሮክ በሕ​ዝቡ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ በአ​ነ​በበ ጊዜ የሰ​ማ​ውን ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች