Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ፣ ዐይነ ስውር ወደ ነበረው ሰው ተመልሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው፣ እንግዲህ አንተ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም፣ “እርሱ ነቢይ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከዚህም የተነሣ ዐይነ ሥውሩን፥ “አንተ ዐይኖችህን ስለ ከፈተ፥ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም “ነቢይ ነው፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ ዕውር የነበረውን ሰው፥ “አንተስ ዐይኖችህን አበራልኝ ስለምትለው ስለዚያ ሰው ምን ትላለህ?” ሲሉ ደግመው ጠየቁት። እርሱም “ነቢይ ነው!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ “አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም፦ “ነቢይ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 9:17
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በቃ​ሉና በሥ​ራው ብርቱ ነቢ​ይና እው​ነ​ተኛ ሰው ስለ​ነ​በ​ረው ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ፥


ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ።


ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው።


ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች