Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 8:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የምናገረውን ለምን አታስተውሉም? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ስለ ምን ንግግሬ አይገባችሁም? ንግግሬን ለመስማት ስለማትችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 8:43
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አያ​ው​ቁም፤ አያ​ስ​ቡም፤ እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልቦ​ቻ​ቸው ተጋ​ር​ደ​ዋል።


እር​ሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፥ አታ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፥ አት​መ​ለ​ከ​ቱ​ምም” በላ​ቸው አለኝ።


ይሰ​ሙ​ኝስ ዘንድ ለማን እና​ገ​ራ​ለሁ? ለማ​ንስ አዳ​ኛ​ለሁ? እነሆ፥ ጆሮ​አ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዘች ናት፤ ለመ​ስ​ማ​ትም አይ​ች​ሉም፤ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ለስ​ድብ ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፥ ይሰ​ሙት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ምና።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፥ እንደ ነዶ ወደ አውድማ አከማችቶአቸዋልና።


በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


እኔ በአ​ባቴ ስም መጣሁ፥ አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምም፤ ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ እር​ሱን ትቀ​በ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ።


ፈቃ​ዱን ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ወ​ድድ ግን ትም​ህ​ርቴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የም​ና​ገ​ረ​ውም ከራሴ እን​ዳ​ይ​ደለ እርሱ ያው​ቃል።


ነገር ግን ስለ አብ እንደ ነገ​ራ​ቸው አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “እኛ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማ​ንም ከቶ ባሮች አል​ሆ​ንም፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አር​ነት ትወ​ጣ​ላ​ችሁ ትለ​ና​ለህ?” አሉት።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “የእ​ኛስ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ነው” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ብት​ሆ​ኑስ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሥራ በሠ​ራ​ችሁ ነበር።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


አስ​ተ​ዋ​ይም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ሻው የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች