Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 8:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “የእ​ኛስ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ነው” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ብት​ሆ​ኑስ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሥራ በሠ​ራ​ችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እነርሱም፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” ብለው መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ፣ አብርሃም የሠራውን ትሠሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 መልሰውም “አባታችንስ አብርሃም ነው፤” አሉት። ኢየሱስም “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑማ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 እነርሱም “አባታችን አብርሃም ነው” ሲሉ መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 መልሰውም፦ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስም፦ “የአብሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 8:39
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “እኛ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማ​ንም ከቶ ባሮች አል​ሆ​ንም፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አር​ነት ትወ​ጣ​ላ​ችሁ ትለ​ና​ለህ?” አሉት።


የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንደ ሆና​ች​ሁስ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ኖ​ር​ምና ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ።


እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።


አባ​ታ​ችሁ አብ​ር​ሃም የእ​ኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤ አይ​ቶም ደስ አለው።”


ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ።


የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ።


ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።


እን​ግ​ዲህ ያመ​ኑት የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች