Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሕዝ​ቡም ስለ እርሱ ብዙ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይ​ደ​ለም፤ ሕዝ​ቡን ያስ​ታል እንጂ” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለ እርሱ በሕዝቡ መካከል ብዙ ጕምጕምታ ነበር። አንዳንዶች፣ “ደግ ሰው ነው” አሉ። ሌሎች ግን፣ “የለም፤ ሕዝቡን የሚያስት ነው” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሕዝቡም መካከል በእርሱ ምክንያት ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዶቹ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ ሕዝቡን ያስታል እንጂ፤” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝቡም ስለ እርሱ በሹክሹክታ ይነጋገሩ ነበር፤ አንዳንዶቹ “እርሱ ደግ ሰው ነው” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ እርሱ ሕዝቡን ያስታል” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሕዝቡም መካከል ስለ እርሱ ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዱም፦ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ግን፦ “አይደለም፥ ሕዝቡን ግን ያስታል” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 7:12
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ን​ዶች፥ “ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ሰን​በ​ትን አያ​ከ​ብ​ር​ምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው እን​ዲህ ያለ ተአ​ም​ራት ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?” አሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተለ​ያዩ።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ን​ተም ደግሞ ተሳ​ሳ​ታ​ች​ሁን?


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።


የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ።


ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ።


ደግ ሰው፥ መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት፥ ሃይ​ማ​ኖ​ተ​ኛም ነበ​ርና፤ በጌ​ታ​ች​ንም አም​ነው ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ተጨ​መሩ።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።


ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።


እነሆ፥ በጎና ጻድቅ ሰው፥ የሸ​ንጎ አማ​ካ​ሪም የሆነ ዮሴፍ የሚ​ባል ሰው መጣ።


የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ለምን ቸር ትለ​ኛ​ለህ? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ቸር የለም።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።


ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች