Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወን​ድ​ሞቹ ለበ​ዓል ከወጡ በኋላ፥ እር​ሱም ያን​ጊዜ በግ​ልጥ ሳይ​ሆን ተሰ​ውሮ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይሁን እንጂ፣ ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ፣ እርሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ፥ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነገር ግን ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እርሱ በይፋ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ በዚያን ጊዜ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 7:10
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


ከዚ​ያም ወዲያ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል በግ​ልጥ አል​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለም​ድረ በዳ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍ​ሬም ወደ​ም​ት​ባል ከተማ ሄደ፤ በዚ​ያም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ተቀ​መጠ።


ወን​ድ​ሞቹ ገና አላ​መ​ኑ​በ​ትም ነበ​ርና።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።


ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።


የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?


ልቤ አን​ተን አለ፦ ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥ አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።


ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


ዘመዶቹም ሰምተው “አበደ” ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።


እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸው በገ​ሊላ ቀረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች