Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ በዚያ የነበሩት አይሁድ ሊገድሉት ስለ ፈለጉ፣ በይሁዳ አውራጃ መዘዋወር ትቶ በገሊላ ተዘዋወረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ይመላለስ ነበር። አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ይዘዋወር ነበር፤ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበረ ግን በይሁዳ ሊዘዋወር አልፈለገም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 7:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።


የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ምድር ትቶ ዳግ​መኛ ወደ ገሊላ ሄደ።


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደ​ረ​ገው ሁለ​ተ​ኛው ተአ​ምር ይህ ነው።


ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ።


አይ​ሁ​ድም፥ “ያ ወዴት ነው?” እያሉ በበ​ዓሉ ይፈ​ል​ጉት ጀመር።


ነገር ግን፥ አይ​ሁ​ድን በመ​ፍ​ራት የእ​ር​ሱን ነገር ገልጦ የተ​ና​ገረ አል​ነ​በ​ረም።


ሙሴ ኦሪ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ የለ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ ኦሪ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ እን​ግ​ዲህ ልት​ገ​ድ​ሉኝ ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?”


ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎ​ችም እን​ዲህ የሚሉ ነበሩ፥ “ይህ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት የሚ​ሹት አይ​ደ​ለ​ምን?


አይ​ሁ​ድም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ አሉ፥ “እኛ ልና​ገ​ኘው የማ​ን​ችል ይህ ወዴት ይሄ​ዳል? ወይስ የግ​ሪ​ክን ሰዎች ለማ​ስ​ተ​ማር በግ​ሪክ ሀገር ወደ ተበ​ተ​ኑት ይሄ​ዳ​ልን?


የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንደ ሆና​ች​ሁስ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ኖ​ር​ምና ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም።


ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች