Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:62 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

62 እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

62 ታዲያ፣ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

62 ታዲያ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ሊሆን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

62 የሰው ልጅ ወደነበረበት ተመልሶ ሲወጣ ስታዩ ምን ልትሉ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

62 እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲመጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:62
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው።


ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ።


ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”


እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤


ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው።


የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።”


“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የሰ​ውን ልጅ ሥጋ ካል​በ​ላ​ችሁ፥ ደሙ​ንም ካል​ጠ​ጣ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የላ​ች​ሁም።


ይህ​ንም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመ​ናም ተቀ​በ​ለ​ችው፤ እነ​ር​ሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ተሰ​ወረ።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች