Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በማ​ግ​ሥ​ቱም ከባ​ሕሩ ዳር ቆመው የነ​በሩ ሰዎች ከአ​ን​ዲት ታንኳ በቀር ከዚያ ሌላ ታንኳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለብ​ቻ​ቸው ሄዱ እንጂ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ እን​ዳ​ል​ወጣ አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በማግስቱም በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች በዚያ አንዲት ጀልባ ብቻ እንደ ነበረች ተረዱ፤ ኢየሱስ እንዳልተሳፈረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱም ዐወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በማግሥቱም በባሕር ማዶ ቆሞ የነበረው ሕዝብ ከአንዲት ጀልባ በቀር በዚያ ሌላ ጀልባ እንዳልነበረች፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው እንደ ሄዱ እንጂ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ እንዳልገባ አዩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በማግስቱ ከባሕሩ ማዶ ቀርተው የነበሩት ሰዎች፥ በባሕሩ ላይ አንድ ጀልባ ብቻ እንደ ነበረና በዚያም ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱ፥ ኢየሱስ ግን ከእነርሱ ጋር ወደ ጀልባዋ እንዳልገባ አይተው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በነገው በባሕር ማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝቡ ከአንዲት ጀልባ በቀር በዚያ ሌላ ጀልባ እንዳልነበረች፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው እንደ ሄዱ እንጂ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ እንዳልገባ አዩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:22
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች