Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 5:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 “በመ​ቃ​ብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚ​ሰ​ሙ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለ​ችና ስለ​ዚህ አታ​ድ​ንቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “በዚህ አትደነቁ፤ መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በዚህ አታድንቁ፤ በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚህ ነገር አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉት ሁሉ የእርሱን ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28-29 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 5:28
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።


ስለ​ዚ​ህም ዳግ​መኛ ልት​ወ​ለዱ ይገ​ባ​ች​ኋል ስለ አል​ሁህ አታ​ድ​ንቅ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ።


ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም ለጻ​ድ​ቃ​ንና ለኃ​ጥ​ኣን የሙ​ታን ትን​ሣኤ ይሆን ዘንድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ለእ​ኔም እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ተስፋ አለኝ።


ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?


ሁሉ በአ​ዳም እን​ደ​ሚ​ሞት እን​ዲሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉ ሕያ​ዋን ይሆ​ናሉ።


እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።


ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች