Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አሳ​ዳ​ሪ​ውም ያን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ውኃ ቀምሶ አደ​ነቀ፤ ከወ​ዴት እንደ መጣም አላ​ወ​ቀም፤ የቀ​ዱት አሳ​ላ​ፊ​ዎች ግን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃ​ዉን የሞሉ እነ​ርሱ ነበ​ሩና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የድግሱ ኀላፊም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር። እርሱም ሙሽራውን ለብቻው ጠርቶ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የግብዣው ኀላፊ ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ፥ ከየት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ ስለዚህ የግብዣው ኀላፊ፥ ሙሽራውን ጠርቶ እንዲህ አለው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 2:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤


ፈቃ​ዱን ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ወ​ድድ ግን ትም​ህ​ርቴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የም​ና​ገ​ረ​ውም ከራሴ እን​ዳ​ይ​ደለ እርሱ ያው​ቃል።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።


በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።


“አሁ​ንም ቅዱና ወስ​ዳ​ችሁ ለአ​ሳ​ዳ​ሪው ስጡት” አላ​ቸው፤ ወስ​ደ​ውም ሰጡት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች