Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አስቀድሜ ይህን የነገርኋችሁ ጊዜው ሲደርስ እንድታስታውሱ ነው፤ ከእናንተ ጋራ ስለ ነበርሁ፣ ይህን ከመጀመሪያው አልነገርኋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይህንን ለእናንተ መናገሬ ግን ጊዜው ሲደርስ ምን እንዳልኳችሁ እንድታስታውሱ ነው።” “ይህን ሁሉ ከአሁን በፊት ያልነገርኳችሁ ከእናንተ ጋር ስለ ነበርኩ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግራአችኋለሁ። ከእንናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 16:4
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም ይህ በሆነ ጊዜ ታምኑ ዘንድ አስ​ቀ​ድሜ ሳይ​ሆን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።


እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።


በሆ​ነም ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከዛሬ ጀምሮ ከመ​ሆኑ አስ​ቀ​ድሞ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።


ኢየሱስም አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጾሙ አይችሉም።


እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ አካሌ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና።


እኔም ስለ ስሜ መከ​ራን ይቀ​በል ዘንድ እን​ዳ​ለው አሳ​የ​ዋ​ለሁ።”


ሄዳችሁም ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች፤’ ብላችሁ ስበኩ።


ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤


ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች