Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 16:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ በየ​ቦ​ታዉ የም​ት​በ​ታ​ተ​ኑ​በት፥ እኔ​ንም ብቻ​ዬን የም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ ይደ​ር​ሳል፤ ደር​ሶ​አ​ልም፤ እኔ ግን ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋራ ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 16:32
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና፤


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፤” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


ኢየሱስም “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛዉን እመታለሁ፤ በጎችም ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “አሁን የሰው ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ጊዜው ደረሰ።


ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል።


“ዛሬስ በም​ሳሌ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን የአ​ብን ነገር ገልጬ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ለእ​ና​ንተ በም​ሳሌ የማ​ል​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ይመ​ጣል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ታም​ና​ላ​ች​ሁን?


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት።


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ተመ​ል​ሰው ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ።


ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


“በመ​ቃ​ብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚ​ሰ​ሙ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለ​ችና ስለ​ዚህ አታ​ድ​ንቁ።


እኔ ብፈ​ር​ድም እው​ነ​ትን እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔና የላ​ከኝ አብ ነን እንጂ አንድ ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።


የላ​ከ​ኝም ከእኔ ጋር አለ፤ አብ ብቻ​ዬን አይ​ተ​ወ​ኝም፤ እኔም ዘወ​ትር ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን አደ​ር​ጋ​ለሁ።”


እርስ በር​ሳ​ች​ንም ተሳ​ስ​መን ተሰ​ነ​ባ​በ​ትን፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ መር​ከብ ወጣን፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።


በዚያ ወራ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትም በቀር ሁሉም በይ​ሁ​ዳና በሰ​ማ​ርያ ባሉ አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ተበ​ተኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች