Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 16:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “ዛሬስ በም​ሳሌ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን የአ​ብን ነገር ገልጬ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ለእ​ና​ንተ በም​ሳሌ የማ​ል​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ይመ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “እስከ አሁን የነገርኋችሁ በምሳሌ ቢሆንም እንኳ፣ ከእንግዲህ ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጥ ለእናንተ የምናገርበት ሰዓት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እስከ አሁን በምሳሌ ነገርኳችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ስለ አብ ሁሉን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 16:25
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በላይ ያለ​ውን ሰማ​ይን ምድ​ር​ንም በሕ​ዝቡ ለመ​ፍ​ረድ ይጠ​ራል፥


የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም በድ​ኖች ለሰ​ማይ ወፎች መብል አደ​ረጉ፥ የጻ​ድ​ቃ​ን​ህ​ንም ሥጋ ለም​ድር አራ​ዊት፤


ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።


እኔም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ አይ​ሁን አልሁ፤ እነ​ርሱ ግን፦ ይህ የነ​ገ​ረን ምሳሌ አይ​ደ​ለ​ምን? ይሉ​ኛል።”


አላቸውም “ይህን ምሳሌ አታውቁምን? እንዴትስ ምሳሌዎቹን ሁሉ ታውቃላችሁ?


ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።


ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።


አይ​ሁ​ድም እር​ሱን ከብ​በው፥ “እስከ መቼ ድረስ ሰው​ነ​ታ​ች​ንን ታስ​ጨ​ን​ቀ​ና​ለህ? አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ ገል​ጠህ ንገ​ረን” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ምሳሌ ነገ​ራ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁም።


“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም።


ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል።


እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ በየ​ቦ​ታዉ የም​ት​በ​ታ​ተ​ኑ​በት፥ እኔ​ንም ብቻ​ዬን የም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ ይደ​ር​ሳል፤ ደር​ሶ​አ​ልም፤ እኔ ግን ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች