Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “እናትና አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም፤ ተመልሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 14:18
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።


ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥ በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።


አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።


እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?


ድሀ-አደ​ጎች ሆነ​ናል፤ አባ​ትም የለ​ንም። እና​ቶ​ቻ​ችን እንደ መበ​ለ​ቶች ሆነ​ዋል።


ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”


እኔም አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ና​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽ​ናኝ ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።”


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።


እርሱ ራሱ ተፈ​ትኖ መከ​ራን ስለ ተቀ​በለ የሚ​ፈ​ተ​ኑ​ትን ሊረ​ዳ​ቸው ይች​ላ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች