ዮሐንስ 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው “ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ፥ የእስራኤልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥተው ተቀበሉት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የዘንባባም ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ሆሳዕና!” “በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው!” “የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዞ ሊቀበለው ወጣና “ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፤” እያሉ ጮኸ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ስለዚህ የዘንባባ ቅርንጫፍ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” እያሉ ይጮኹ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ “ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው” እያሉ ጮኹ። ምዕራፉን ተመልከት |