Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሕያው የሆነ የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሞ​ትም፤ ይህ​ንስ ታም​ኛ​ለ​ሽን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሕያው የሆነና በእኔ የሚያምን ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽኝ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በሕይወት የሚኖርና በእኔም የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሕያው የሆነም የሚያምንብኝ ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽኝ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይችል ይመስልሃልን?


ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት።


ኢየሱስም “ቢቻልህ ትላለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፤” አለው።


እኔም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ጠ​ፉም፤ ከእ​ጄም የሚ​ነ​ጥ​ቃ​ቸው የለም።


እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ አታ​ም​ን​ምን? እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይህ ቃልም ከራሴ የተ​ና​ገ​ር​ሁት አይ​ደ​ለም፤ በእኔ ያለ አብ እርሱ ይህን ሥራ ይሠ​ራ​ዋል እንጂ።


እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ሰማ በላ​ከ​ኝም የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያገ​ኛል፤ ከሞ​ትም ወደ ሕይ​ወት ተሻ​ገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይ​ሄ​ድም።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ውጭ እን​ዳ​ወ​ጡት ሰማ፤ አገ​ኘ​ው​ምና፥ “አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ታም​ና​ለ​ህን?” አለው።


እንደ ሥጋ ፈቃድ ብት​ኖሩ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ ብት​ገ​ድሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች