Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 1:9
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ነገ​ዶች እን​ደ​ገና እን​ድ​ታ​ስ​ነሣ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ወደ አባ​ቶች ቃል ኪዳን እን​ድ​ት​መ​ልስ ባር​ያዬ ትሆን ዘንድ ለአ​ንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ይላል።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!


ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነ በአ​ን​ተም ላይ ምንም ጨለማ ባይ​ኖ​ር​ብህ የመ​ብ​ረቅ ብር​ሃን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ራ​ልህ ሁለ​ን​ተ​ናህ ብሩህ ይሆ​ናል።”


ሕይ​ወት በእ​ርሱ ነበረ፥ ሕይ​ወ​ትም የሰው ብር​ሃን ነበረ፤


እር​ሱም ሁሉ በእ​ርሱ በኩል እን​ዲ​ያ​ምን ስለ ብር​ሃን ይመ​ሰ​ክር ዘንድ ለም​ስ​ክ​ር​ነት መጣ።


በእኔ የሚ​ያ​ምን ሁሉ በጨ​ለማ እን​ዳ​ይ​ኖር ብር​ሃን እኔ ወደ ዓለም መጣሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያን እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሰ​ጣ​ችሁ ሙሴ አይ​ደ​ለም፤ አባቴ ከሰ​ማይ የእ​ው​ነት እን​ጀ​ራን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል እንጂ።


ሕዝ​ቡም ስለ እርሱ ብዙ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይ​ደ​ለም፤ ሕዝ​ቡን ያስ​ታል እንጂ” አሉ።


ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።


ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች