Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ድም​ፃ​ቸ​ውም በተ​ራራ ላይ እንደ አሉ ሠረ​ገ​ሎች ድምፅ፥ ገለ​ባ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​በላ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ድምፅ ነው፤ ለሰ​ል​ፍም እንደ ተዘ​ጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራ​ዊት ያኰ​በ​ኵ​ባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣ የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘልላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኩባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንደ ሠረገላ ድምፅ እያሰሙ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ፤ ገለባን እንደሚያቃጥል እሳትም፥ ሁሉን ነገር ያቃጥላሉ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ብርቱ ሠራዊት በሰልፍ ይተማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኵባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፍ​ጹም የጦር መሣ​ሪያ አስ​ጊ​ጠ​ኸ​ዋ​ልን? እም​ቢ​ያ​ው​ንስ በብ​ር​ታት የከ​በረ አድ​ር​ገ​ኸ​ዋ​ልን?


ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች