Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ እህ​ል​ንና ወይ​ንን፥ ዘይ​ት​ንም እሰ​ድ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በእ​ርሱ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል መሰ​ደ​ቢያ አላ​ደ​ር​ጋ​ች​ሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እልክላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አሕዛብ መዘባበቻ እንዲያደርጉአችሁ አልፈቅድም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:19
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰ​ላ​ምን ተክል አቆ​ም​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከራብ የተ​ነሣ በም​ድር አያ​ል​ቁም፤ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ሸ​ከ​ሙም።


ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ አላ​ሰ​ማ​ብ​ሽም፤ ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ውር​ደት አት​ሸ​ከ​ሚም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን አታ​ሰ​ና​ክ​ዪም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ዐው​ድ​ማ​ዎ​ችም እህ​ልን ይሞ​ላሉ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ዎ​ችም የወ​ይን ጠጅ​ንና ዘይ​ትን አት​ረ​ፍ​ር​ፈው ያፈ​ስ​ሳሉ።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


እር​ሻው ምድረ በዳ ሆኖ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም ታል​ቅስ፤ እህሉ ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ ወይ​ኑም ደር​ቆ​አ​ልና፥ ዘይ​ቱም ጐድ​ሎ​አ​ልና።


ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።


ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​መ​ል​ስም፤ መዓ​ቴን በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ላይ አፍ​ስ​ሻ​ለ​ሁና፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ህ​ሉም ማበ​ራ​የት በእ​ና​ንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቈ​ረጥ ይደ​ር​ሳል፤ የወ​ይ​ኑም መቈ​ረጥ እስከ እህሉ መዝ​ራት ይደ​ር​ሳል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤


ምድ​ርም ለእ​ህል፥ ለወ​ይ​ንና ለዘ​ይት ትመ​ል​ሳ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይመ​ል​ሳሉ።


እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ትሰ​በ​ስብ ዘንድ በየ​ጊ​ዜው የበ​ል​ጉን ዝና​ብና የክ​ረ​ም​ቱን ዝናብ ለም​ድ​ርህ ይሰ​ጣል።


እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።


ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።


ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች