Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወይ​ኔን ባዶ ምድር አደ​ረ​ገው፤ በለ​ሴ​ንም ሰበ​ረው፤ ተመ​ለ​ከ​ተ​ውም፥ ጣለ​ውም፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ነጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የወይን ቦታዬን ባድማ አደረገው፤ የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስኪታዩ ድረስ፣ ቅርፊታቸውን ልጦ፣ ወዲያ ጣላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የወይን ተክሎቼን ሁሉ አጠፋ፤ የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስከሚታዩ ድረስ፥ ቅርፊቱን ልጦ ጣለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 1:7
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መን​ፈ​ሱን አስ​መ​ር​ረ​ዋ​ታ​ልና፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቹም አዘዘ።


አን​በ​ጣም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግ​ብ​ፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀ​መጠ፤ እጅ​ግም ብዙና ጠን​ካራ ነበር፤ ይህ​ንም የሚ​ያ​ህል አን​በጣ በፊት አል​ነ​በ​ረም፤ ወደ​ፊ​ትም ደግሞ እንደ እርሱ አይ​ሆ​ንም።


የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ፈጽሞ ሸፈ​ነው፤ ሀገ​ሪ​ቱም ጠፋች፤ የሀ​ገ​ሪ​ቱን ቡቃያ ሁሉ ከበ​ረ​ዶ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን፥ በዛፉ የነ​በ​ረ​ውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለም​ለም ነገር በዛ​ፎች ላይ፥ በእ​ር​ሻ​ውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ አል​ቀ​ረም።


የወ​ይን ጠጅ አለ​ቀ​ሰች፤ የወ​ይን ግንድ ደከ​መች፤ ልባ​ቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።


ስለ ተወ​ደ​ደ​ችዉ እርሻ ስለ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ውም ወይን ደረ​ታ​ች​ሁን ድቁ።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በወ​ይን ላይ ፍሬ፥ በበ​ለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠ​ልም ይረ​ግ​ፋል፤ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ አለ​ፈ​ባ​ቸ​ውም።


እር​ስ​ዋም፥ “ወዳ​ጆች የሰ​ጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለ​ች​ውን ሁሉ ወይ​ን​ዋ​ንና በለ​ስ​ዋን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ይሆኑ ዘንድ አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊ​ትና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ይበ​ሉ​ታል።


ወይኑ ደር​ቆ​አል፤ በለ​ሱም ጠፍ​ቶ​አል፤ ሮማ​ኑና ተምሩ፥ እን​ኮ​ዩም፥ የም​ድ​ርም ዛፎች ሁሉ ደር​ቀ​ዋል፤ ደስ​ታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆ​አል።


በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች