ኢዩኤል 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እናንተ ሰካራሞች፥ ንቁ፤ ለመስከርም ወይንን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍትዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 አዲስ የወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ የወይን ጠጅ በአፋችሁ ስለማትቀምሱ፥ እናንተ ሰካራሞች ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ መጠጣት የምታዘወትሩ ምርር ብላችሁ አልቅሱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በተሃ ወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ። ምዕራፉን ተመልከት |