Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እር​ሱም በጥ​ፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ወዮ ለዚያ ቀን! የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ ከሁሉን ቻይ አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የጌታ ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ወዮ! የጌታ ቀን ቀርቦአል! ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ደርሶአል። ስለዚያ ቀን ወዮ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 1:15
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል የለ​ምና፤ ያ የያ​ዕ​ቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ይድ​ናል።


ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።


ወንድሞች ሆይ! እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።


እኔ ግን እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ደን​ቆሮ፥ አፉ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ፍት ዲዳ ሆንሁ።


ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።


ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ቀር​ቦ​አ​ልና፥ አንተ እንደ አደ​ረ​ግ​ኸው እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ብ​ሃል፤ ፍዳ​ህም በራ​ስህ ላይ ይመ​ለ​ሳል።


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች