Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 መከሩ ከእ​ር​ሻ​ቸው ጠፍ​ቶ​አ​ልና ገበ​ሬ​ዎች ስለ ስን​ዴ​ውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞ​ችም ስለ ወይኑ አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እናንተ ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤ እናንተ የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤ የዕርሻው መከር ጠፍቷልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 መከሩ ከእርሻ ጠፍቶአልና ገበሬዎች ሆይ፥ ስለ ስንዴውና ስለ ገብሱ እፈሩ፥ የወይን አትክልተኞችም አልቅሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስንዴውና ገብሱ፥ ሌላውም መከር ሁሉ ስለ ጠፋ፥ እናንተ ገበሬዎች እዘኑ፤ እናንተም የወይን ተክል ባለቤቶች አልቅሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 መከሩ ከእርሻቸው ጠፍቶአልና ገበሬዎች ስለ ስንዴውና ስለ ገብሱ አፈሩ፥ የወይን አትክልተኞችም አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 1:11
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተክ​ልን በተ​ከ​ል​ህ​በት ቀን ትበ​ድ​ላ​ለህ፤ የዘ​ራ​ኸ​ውም በበ​ነ​ጋው በም​ታ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ይበ​ቅ​ላል፤ አባ​ትም ለልጁ እን​ደ​ሚ​ያ​ወ​ርስ አን​ተም ለል​ጆ​ችህ ታወ​ር​ሳ​ለህ።


ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?


ተስ​ፋም አያ​ሳ​ፍ​ርም፤ በሰ​ጠን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በል​ባ​ችን መል​ቶ​አ​ልና።


ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ።


ዘሪ​ው​ንና በመ​ከር ጊዜ ማጭድ የሚ​ይ​ዘ​ውን ከባ​ቢ​ሎን አጥፉ፤ ከአ​ረ​ማ​ዊው ሰይፍ ፊት የተ​ነሣ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥ ለቀኑ ወዮ!


ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች