ኢዮብ 39:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በከተማው ሕዝብ ውካታ ይዘብታል፤ የሚያስፈራውንም ጩኸት አይሰማም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 በከተማ ውካታ ይሥቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በከተማ ውካታ ይስቃል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ሁካታ ከበዛባቸው ከተሞች ርቀው ይኖራሉ፤ ከኋላ እየነዳ የሚጮኽባቸውን አይቀበሉም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በከተማ ውካታ ይዘብታል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። ምዕራፉን ተመልከት |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።