Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሽመላ በሰ​ማይ ጊዜ​ዋን አው​ቃ​ለች፤ ዋኖ​ስና ጨረባ፥ ዋሊ​ያም የመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውን ጊዜ ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ አላ​ወ​ቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሽመላ እንኳ በሰማይ፣ የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፤ ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣ የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንዲሁም ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጫቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የጌታን ፍርድ አላወቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሽመላዎች እንኳ የሚመለሱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ዋኖሶች፥ ጨረባዎች፥ ዋርዳዎችም በኅብረት የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ እናንተ ሕዝቤ ግን እንድትተዳደሩበት የሰጠኋችሁን ሕግ አታውቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፥ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፥ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 8:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሬ ገዢ​ውን አህ​ያም የጌ​ታ​ውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስ​ራ​ኤል ግን አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ሕዝ​ቤም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ኝም።”


በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በከ​በ​ሮና በእ​ም​ቢ​ል​ታም እየ​ዘ​ፈኑ የወ​ይን ጠጅን ይጠ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ቱም፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


አበባ በም​ድር ላይ ታየ፥ የመ​ከ​ርም ጊዜ ደረሰ፥ የቍ​ር​ዬ​ውም ቃል በም​ድ​ራ​ችን ተሰማ።


ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።


ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፣ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፣ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።


የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፥ የዐ​መ​ፃ​ቸ​ውም ብዛት ጸን​ቶ​አ​ልና አን​በሳ ከዱር ወጥቶ ይሰ​ብ​ራ​ቸ​ዋል፤ የበ​ረ​ሃም ተኵላ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ነብ​ርም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ ይተ​ጋል፤ ከዚ​ያም የሚ​ወጣ ሁሉ ይነ​ጠ​ቃል።


ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፣ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፣ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች