Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ይህ ስሜ የተ​ጠ​ራ​በት ቤት በዐ​ይ​ና​ችሁ የሌ​ቦች ዋሻ ነውን? እነሆ፥ እኔ አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስሜ የሚጠራበት፣ ይህ ቤት በእናንተ ዘንድ የወንበዴዎች ዋሻ ሆኗልን? እነሆ፤ የምታደርጉትን ነገር አይቻለሁ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ ራሴ አይቻለሁ፥ ይላል ጌታ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ቤተ መቅደሴ የሌቦች መደበቂያ ዋሻ መሰላችሁን? የምታደርጉትን ሁሉ እነሆ እኔ ራሴ አይቼአለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 7:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።


“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።


አስተማራቸውም “‘ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።


አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብ​ህም እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


ርግብ ሻጮ​ች​ንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአ​ባ​ቴን ቤት የን​ግድ ቤት አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሚስ​ቶች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ያላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ቃል በስሜ በሐ​ሰት ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና። እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


በእ​ጆ​ች​ሽም የን​ጹ​ሓን ድሆች ደም ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግ​ልጥ አገ​ኘ​ሁት እንጂ በጕ​ድ​ጓድ ፈልጌ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።


መጥ​ታ​ች​ሁም ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት በዚህ ቤት በፊቴ ብት​ቆሙ፦ ይህን አስ​ጸ​ያፊ የሆነ ነገ​ርን ሁሉ ከማ​ድ​ረግ ተለ​ይ​ተ​ናል ብትሉ፥


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


በእኔ ፊት ልት​ታዩ ብት​መጡ፥ ይህን ከእ​ጃ​ችሁ የሚሻ ማን ነው? እን​ግ​ዲህ አደ​ባ​ባ​ዬን ደግ​ማ​ችሁ አት​ረ​ግ​ጡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች