Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 52:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የማ​ረ​ከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይ​ሁድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰደው ሕዝብ ቍጥር እንደሚከተለው ነው፦ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣ ሦስት ሺሕ ሃያ ሦስት አይሁድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ናቡከደነፆር ማርኮ ያፈለሰው የሕዝብ ቍጥር ብዛት ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ብዛት ማስታወሻ ይህ ነው፤ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ የማረካቸው ሦስት ሺህ ኻያ ሦስት አይሁድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፥ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 52:28
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተ​ረ​ፉ​ት​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው፤ የሜ​ዶ​ንም ንጉሥ እስ​ኪ​ነ​ግሥ ድረስ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆቹ ባሪ​ያ​ዎች ሆኑ፤


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


የደ​ቡብ ከተ​ሞች ተዘ​ግ​ተ​ዋል፤ የሚ​ከ​ፍ​ታ​ቸ​ውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተሰ​ድ​ዶ​አል፤ ፈጽ​ሞም ተሰ​ድ​ዶ​አል።


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስም​ንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማር​ኮ​አል፤


ሄ። ስለ ኀጢ​አቷ ብዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ታ​ልና የሚ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባት በራ​ስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላ​ቶ​ች​ዋም ተደ​ሰቱ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ች​ዋም በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ፊት ተማ​ር​ከ​ዋል።


ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች