Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 51:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 “የም​ድ​ርም ሁሉ ክብር እን​ዴት ተያ​ዘች! እን​ዴ​ትስ ተወ​ሰ​ደች! ባቢ​ሎን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆነች!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 “ሼሻክ እንዴት ተማረከች! የምድር ሁሉ ትምክሕትስ እንዴት ተያዘች! ባቢሎን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ፣ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ሼሻክ እንዴት ተያዘች! ምድርም ሁሉ የሚያመሰግናት እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መሣቀቅያ እንዴት ሆነች!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ከተማ እንዴት ተወረረች! ያቺ የዓለም መመኪያ የነበረችው እርስዋ እንዴት ተያዘች! ባቢሎንስ በሕዝብ ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ሼሻክ እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 51:41
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቀ​ረ​ቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌ​ላው ጋር ያሉ የሰ​ሜን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ የዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው፤ የሲ​ሳ​ርም ንጉሥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ይጠ​ጣል።


የመ​ን​ግ​ሥ​ታት ክብር፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም የት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ትም​ክ​ሕት የሆ​ነች ባቢ​ሎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ትሆ​ና​ለች።


የወ​ደ​ዱ​ትን ቦታና ከተማ እን​ዴት አል​ተ​ዉ​ላ​ትም?


በደ​ሴ​ቶች የሚ​ኖሩ ሁሉ አለ​ቀ​ሱ​ልሽ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅግ ፈር​ተ​ዋል ፊታ​ቸ​ው​ንም ነጭ​ተው አለ​ቀሱ።


ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም።


ባቢ​ሎ​ንን ከያ​ዝ​ዋት ሰዎች ድምፅ የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ጩኸ​ትም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተሰማ።”


ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች!


ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ!


ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ው​ንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚ​ያ​ልፍ መን​ገ​ደኛ ሁሉ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ?’ ብሎ ይደ​ነ​ቃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች