Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 50:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዘሪ​ው​ንና በመ​ከር ጊዜ ማጭድ የሚ​ይ​ዘ​ውን ከባ​ቢ​ሎን አጥፉ፤ ከአ​ረ​ማ​ዊው ሰይፍ ፊት የተ​ነሣ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣ በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤ ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤ ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ዘሪውንና መከር ሰብሳቢውን ከባቢሎን አስወግዱ፤ በዚያች አገር የሚኖር እያንዳንዱ የውጪ ዜጋ አደጋ የሚጥልባትን ሠራዊት በመፍራት ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 50:16
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተ​ረ​ፉ​ትም ሁሉ እንደ ተባ​ረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆ​ናሉ። የሚ​ሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ውም የለም፤ እን​ዲ​ሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።


እንደ አን​በሳ መደ​ቡን ለቅ​ቆ​አል፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰል​ፍና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ ምድ​ራ​ቸው ምድረ በዳ ሆና​ለ​ችና።”


ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው።


በአ​ን​ቺም እረ​ኛ​ው​ንና መን​ጋ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ሹ​ንና ጥማ​ዱን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አለ​ቆ​ች​ንና መሳ​ፍ​ን​ትን እበ​ት​ና​ለሁ።


ባቢ​ሎ​ንን ፈወ​ስ​ናት፥ እር​ስዋ ግን አል​ተ​ፈ​ወ​ሰ​ችም፤ ፍር​ድዋ እስከ ሰማይ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እስከ ከዋ​ክ​ብ​ትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ እን​ተ​ዋት፤ ሁላ​ች​ንም ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ሂድ።


መከሩ ከእ​ር​ሻ​ቸው ጠፍ​ቶ​አ​ልና ገበ​ሬ​ዎች ስለ ስን​ዴ​ውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞ​ችም ስለ ወይኑ አለ​ቀሱ።


ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች