Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 50:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የከ​ላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ትዘ​ረ​ፋ​ለች፤ የማ​ረ​ኳ​ትም ሁሉ ይጠ​ግ​ባሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የባቢሎን ምድር ትዘረፋለች፤ የሚዘርፏትም ሁሉ እስኪበቃቸው ይመዘብሯታል፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች፥ የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ባቢሎን ትመዘበራለች፤ በዝባዥዎችዋም እስከሚበቃቸው ድረስ ያገኙትን ሁሉ ይወስዳሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች፥ የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 50:10
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ገመ​ዶ​ችሽ ተበ​ጥ​ሰ​ዋል፤ ጥን​ካሬ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ደቀ​ልሽ ዘመመ፤ ሸራ​ው​ንም መዘ​ር​ጋት አል​ቻ​ለም፤ እስ​ከ​ሚ​ያ​ዝም ድረስ አላ​ማ​ውን አል​ተ​ሸ​ከ​መም። በዚ​ያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከ​ፈለ፤ ብዙ አን​ካ​ሶች እንኳ ምር​ኮ​ውን ማረኩ።


አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።


በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።


“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።


ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት።


ሰይፍ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም በተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ፤ ሰይፍ በመ​ዝ​ገ​ቦ​ችዋ ላይ አለ፤ ይበ​ተ​ና​ሉም።


በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በራ​እይ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ወደ ምር​ኮ​ኞቹ አመ​ጣኝ።


የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች