Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ቢሉም፣ የሚምሉት በሐሰት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነርሱም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ቢሉም እንኳ የሚምሉት በሐሰት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እናንተ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ በስሜ ትምላላችሁ፤ ነገር ግን የምትምሉት በሐሰት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እነርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 5:2
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ከይ​ሁ​ዳም የወ​ጣ​ችሁ፥ በእ​ው​ነት ሳይ​ሆን፥ በጽ​ድ​ቅም ሳይ​ሆን እር​ሱን እየ​ጠ​ራ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የም​ት​ምሉ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


ስለ​ዚህ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ በሚ​ኖር በይ​ሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ተብሎ እን​ዳ​ይ​ጠራ፥ እነሆ በታ​ላቁ ስሜ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር።


ብት​ገ​ድ​ሉም፥ ብታ​መ​ነ​ዝ​ሩም፥ ብት​ሰ​ር​ቁም፥ በሐ​ሰ​ትም ብት​ምሉ፥ ለበ​አ​ልም ብታ​ጥኑ፥ የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ ክፉ ያገ​ኛ​ች​ኋል።


ሁሉም አመ​ን​ዝ​ሮች፥ የዐ​መ​ጸ​ኞች ጉባኤ ናቸ​ውና ሕዝ​ቤን እተ​ዋ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ር​ሱም እለይ ዘንድ በም​ድረ በዳ ማደ​ሪ​ያን ማን በሰ​ጠኝ?


የማ​ይ​ረ​ባ​ውን የሐ​ሰት ቃል ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል ኪዳ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ ስለ​ዚህ መር​ዛም ሣር በእ​ርሻ ትልም ላይ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ፍርድ ይበ​ቅ​ል​ባ​ቸ​ዋል።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! አንተ አላ​ዋቂ አት​ሁን፤ አን​ተም ይሁዳ! ወደ ጌል​ጌላ አት​ሂድ፤ ወደ ቤት​አ​ዊ​ንም አት​ውጡ፤ በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ማሉ።


በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች