Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 49:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ ግን የዔሳውን ዘር በፍጹም አራቊታቸዋለሁ። የሚሸሸጉበትንም ስፍራ አጋልጣለሁ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ የሚሸሸጉበት ስፍራ ማግኘት አይችሉም፤ ልጆቻቸው፥ ዘመዶቻቸውና ጐረቤቶቻቸው ይጠፋሉ፤ እነርሱም አይኖሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፥ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 49:10
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ሸም ጊዜ ሳይ​ነጋ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ያን​ጊ​ዜም የይ​ሁዳ ወገ​ኖች “ይህ የወ​ራ​ሾች ርስት ነው፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​ንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።


በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።


በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤


ዔሳ​ውን እን​ዴት መረ​መ​ሩት! የሸ​ሸ​ገ​ው​ንም እን​ዴት ወሰ​ዱ​በት!


ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


“ያዕ​ቆ​ብን ወደ​ድሁ፤ ዔሳ​ውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች