Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 48:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ሞአ​ብ​ንም ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም ዕቃ ሰብ​ሬ​አ​ለ​ሁና በሞ​አብ ሰገ​ነት ሁሉ ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፣ በሕዝብም አደባባዮች፣ ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤ እንደማይፈለግ እንስራ፣ ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሞዓብን ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ሰብሬዋለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ሞአብን እንደማይፈለግ ዕቃ ስለ ሰበርኳት በቤት ሰገነቶች ላይና በሕዝብ አደባባዮች ሁሉ ከለቅሶ በቀር ሌላ የሚሰማ ነገር የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ሞዓብን እንደማይወደድ ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 48:38
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


በየ​መ​ን​ገ​ድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየ​ሰ​ገ​ነ​ቶ​ች​ዋም አል​ቅሱ፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ዋም እን​ባን እጅግ እያ​ፈ​ሰ​ሳ​ችሁ ወዮ በሉ።


ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?


አወ​ዳ​ደ​ቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደ​ቀቀ ይሆ​ናል፤ ሳይ​ራ​ራም ያደ​ቅ​ቀ​ዋል፤ ከስ​ባ​ሪ​ውም እሳት ከማ​ን​ደጃ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት፥ ወይም ውኃ ከጕ​ድ​ጓድ የሚ​ቀ​ዱ​በት ገል አይ​ገ​ኝም።”


“ገም​ቦ​ው​ንም ከአ​ንተ ጋር በሚ​ሄዱ ሰዎች ፊት ትሰ​ብ​ራ​ለህ፤


እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።


ኢኮ​ን​ያን ተዋ​ረደ፤ ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም የሸ​ክላ ዕቃ ሆነ፤ እር​ሱ​ንና ዘሩን ወደ​ማ​ያ​ው​ቀው ሀገር ወር​ው​ረው ጥለ​ው​ታ​ልና።


ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።


እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል።


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች