Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 43:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እርሱም መጥቶ ግብጽን ይወጋል፤ ሞት የሚገባቸውን ለሞት፣ ለምርኮ የተመደቡትን ወደ ምርኮ፣ ለሰይፍ የተዳረጉትን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 መጥቶም የግብጽን ምድር ይመታል፥ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን ድል ይነሣል፤ በበሽታ እንዲሞቱ የተወሰነባቸው በበሽታ ይሞታሉ፤ ተማርከው እንዲወሰዱ የተወሰኑ ይማረካሉ፤ በጦርነት እንዲሞቱ የተወሰኑ በጦርነት ይገደላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 መጥቶም የግብጽን ምድር ይመታል፥ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 43:11
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥ ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”


እነ​ር​ሱም፦ ወዴት እን​ሂድ ቢሉህ፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰ​ይ​ፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራ​ብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለም​ር​ኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ያል​ተ​በ​ረዘ የዚ​ህን ቍጣ የወ​ይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አን​ተን የም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ አጠ​ጣ​ቸው።


የግ​ብ​ፅ​ንም ንጉሥ ፈር​ዖ​ንን፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥


አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”


ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን ያቀ​ኑ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ሁሉም ይጠ​ፋሉ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ፤ ከታ​ና​ሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይሞ​ታሉ፤ ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት፥ ለመ​ረ​ገ​ሚ​ያና ለመ​ሰ​ደ​ቢያ ይሆ​ናሉ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በመ​ዐት እንደ ጐበ​ኘሁ፥ እን​ዲሁ በግ​ብፅ ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም እጐ​በ​ኛ​ለሁ።


የሰው እግር አያ​ል​ፍ​ባ​ትም፤ የእ​ን​ስ​ሳም ኮቴ አይ​ረ​ግ​ጣ​ትም፥ እስከ አርባ ዓመ​ትም ድረስ ማንም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፣ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፣ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ።


ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች